ቴዲ አፍሮ
አሁን አይኔ አየ ….የቴዲ አፍሮ የፍቅር ክታብ ! (አሌክስ አብርሃም) .......................................................... ቴዲ አፍሮ ግጥምና ዜማ አቀናጅቶ የሚዘፍን ድምፃዊ ብቻ አይደለም …ቴዲ የነበረውን ታሪክ እየመዘዘ በጎውን ይበል .. መጥፎውንም እንዳይደገም እያለ ከታሪክ ማህደር እኛነታችንን የሚተርክ ንቡር ጠቃሽ ነው ብያችሁ ነበር…ግን ይሄንንም ብቻ አይደለም …ልጁ ከውብ ሴት እግር ስር ተንበርክኮ ‹‹አንች ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት›› አይነት አልፎ ሂያጅ ፍቅር ሰባኪ አይደለም …ቴዲ ለእኔ ፈላስፋም ጭምር ነው …ቀላል ይፈላሰፋል! ያውም ነብስያችን ላይ ነዋ!! በቀደመው ፅሁፌ ‹‹የቴዲ ገፀ ባህሪያት ተራ ሰዎች አይደሉም ለአገራቸው የሚጠበቅባቸውን በሚገባ የተወጡ ምጡቅ ሃላፊነት የሚሰማቸው ነፍሳት ናቸው ›› ብያችሁ ነበር … አሁን አንዷን ገፀ ባህሪ መዝዠ ለዚህ አባባሌ እማኝ ላቀርባት ነው …. በሉ ሙዚቃዋን ከፍ አድርጓትና ጨዋታችንን እንዲህ እንቀጥለው . . . በመጀመሪያ ምደርም ባዶ ነበረ ጨለማም በባዶው ላይ እንዲል ቅዱስ መፅሃፉ የሰው ልጅ ሲፈጠር ባዶ ነው …ሲጀመር የወላጅ ድጋፍ ሲቆይም የቤተሰቡ …የጎረቤቱ …የመንደሩ ….የአገሩ ፍቅር እንደእህል ውሃ በውስጡ ህያውነትን እየገነባ ያሳድገዋል … የሰውን ልጅ ሰፊ ባዶነት መሙላት የሚችል ብቸኛ ተአምር ፍቅር ብቻ ነው ! ሰዎች እየተናቆሩ እየተናከሱ እንኳን አብረው የሚኖሩበትን ከተማ ይመሰርታሉ ለሰው መድሃኒቱ ሰው የመሆኑ ሚስጥር የነፍስያ ሃቅ እንጅ ባዶ ፍልስፍና ወይም አባባል አይደለምና !! ዛሬ ለእኔ የምንግዜም ምርጥ ፍልስፍና የሆነውን የቴዲ አፍሮ አንድ ዘፈን እንደሰማሁት ላሰማችሁ ይሄው ነገሬን ከስሩ ጀመርኩት ! ከዘፍጥረት!! ለምን ከዘ...