Posts

Showing posts from January, 2018

ቴዲ አፍሮ

Image
አሁን አይኔ አየ ….የቴዲ አፍሮ የፍቅር ክታብ !  (አሌክስ አብርሃም) .......................................................... ቴዲ አፍሮ ግጥምና ዜማ አቀናጅቶ የሚዘፍን ድምፃዊ ብቻ አይደለም …ቴዲ የነበረውን ታሪክ እየመዘዘ በጎውን ይበል .. መጥፎውንም እንዳይደገም እያለ ከታሪክ ማህደር እኛነታችንን የሚተርክ ንቡር ጠቃሽ ነው ብያችሁ ነበር…ግን ይሄንንም ብቻ አይደለም …ልጁ ከውብ ሴት እግር ስር ተንበርክኮ ‹‹አንች ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት›› አይነት አልፎ ሂያጅ ፍቅር ሰባኪ አይደለም …ቴዲ ለእኔ ፈላስፋም ጭምር ነው …ቀላል ይፈላሰፋል! ያውም ነብስያችን ላይ ነዋ!! በቀደመው ፅሁፌ ‹‹የቴዲ ገፀ ባህሪያት ተራ ሰዎች አይደሉም ለአገራቸው የሚጠበቅባቸውን በሚገባ የተወጡ ምጡቅ ሃላፊነት የሚሰማቸው ነፍሳት ናቸው ›› ብያችሁ ነበር … አሁን አንዷን ገፀ ባህሪ መዝዠ ለዚህ አባባሌ እማኝ ላቀርባት ነው …. በሉ ሙዚቃዋን ከፍ አድርጓትና ጨዋታችንን እንዲህ እንቀጥለው . . . በመጀመሪያ ምደርም ባዶ ነበረ ጨለማም በባዶው ላይ እንዲል ቅዱስ መፅሃፉ የሰው ልጅ ሲፈጠር ባዶ ነው …ሲጀመር የወላጅ ድጋፍ ሲቆይም የቤተሰቡ …የጎረቤቱ …የመንደሩ ….የአገሩ ፍቅር እንደእህል ውሃ በውስጡ ህያውነትን እየገነባ ያሳድገዋል … የሰውን ልጅ ሰፊ ባዶነት መሙላት የሚችል ብቸኛ ተአምር ፍቅር ብቻ ነው ! ሰዎች እየተናቆሩ እየተናከሱ እንኳን አብረው የሚኖሩበትን ከተማ ይመሰርታሉ ለሰው መድሃኒቱ ሰው የመሆኑ ሚስጥር የነፍስያ ሃቅ እንጅ ባዶ ፍልስፍና ወይም አባባል አይደለምና !! ዛሬ ለእኔ የምንግዜም ምርጥ ፍልስፍና የሆነውን የቴዲ አፍሮ አንድ ዘፈን እንደሰማሁት ላሰማችሁ ይሄው ነገሬን ከስሩ ጀመርኩት ! ከዘፍጥረት!! ለምን ከዘ...

“ይቅርታ ተባሉ፣ አልተባሉ ምን እንዳያመጡ ነው” (ኤፍሬም እንዳለ)

Image
“ይቅርታ ተባሉ፣ አልተባሉ ምን እንዳያመጡ ነው” (ኤፍሬም እንዳለ) በዛ ሰሞን ከአንዳንድ አቅጣጫዎች “ይቅርታ” የሚመስሉ ቃላቶች ሰማን ልበል! ዘንድሮ ነገሮች ሁሉ በቃላት ድሪቶና “እንዲህ የሆነበት ሁኔታ ነው ያለው…” በሚሉ የተለመዱ መቀነቶች ስለመዋጡ ምን እንደተባለና ምን እንዳልተባለ ማወቁም ግራ የሚያጋባ ሆኗል፡፡ ዳኛው ተከሳሹን… “ለፈጸምከው ወንጀል ይቅርታ ከጠየቅህ በግሳጼ ትለቀቃለህ፣” ይሉታል፡፡ “ጌታዬ፣ ምን ብዬ ነው ይቅርታ የምጠይቀው?” “ህብረተሰቡ ላይ ላደረስኩት ችግር ይቅርታ እጠይቃለሁ በላ!” “ጌታዬ አኔ መች ችግር አደረስኩ?” “ህገ ወጥ አልኮል ስታመርት ተይዘሀል፣ አይደል እንዴ!” “እኔ፣ ጌታዬ! በጭራሽ እንደዛ አላደረግሁም፡፡” “በጭራሽ ማለት ምን ማለት ነው! አልኮል ማምረት የሚያስችሉ መሳሪያዎች አሉህ አይደለም እንዴ?” “እንደዛ ከሆነ ጌታዬ በአስገድዶ መድፈርም ይክሰሱኝ፡፡ “ለምን? የሆነች ሴት አስገድደህ ደፍረሀል እንዴ?” “ጌታዬ አልደፈርኩም…ግን እንደዛ ማድረግ የሚያስችል መሳሪያው አለኝ፣” አለና አረፈው፡፡ በእርግጥ ይሄ ለፍርድ ያስቸግራል፡፡ ዘንድሮ እኛ ዘንድ ይቅርታ ሊጠየቅባቸው የሚገቡ በርካታ ጉዳዮች አሉ፡፡ ብዙ ጥፋቶች አሉ…ሆነ ተብለው ከቅንነት ጉድለት የሚፈጸሙ፣ በስልጣን ወይም በሀብት ሽፋን በማን አለብኝነት የሚፈጸሙ፣ ሳናውቅ የምናውቅ እየመሰለን በእውቀት ማነስ የሚፈጸሙ፣ “ሰለሰው፣ ስለሰው ቀድጄ ልልበሰው” በሚል አይነት አመለካከት በግዴለሽነት የሚፈጽሙ፡፡ ምነዋ ታዲያ ይቅርታ ጠያቂዎች አነስን! በነገራችን ላይ… ይቅርታ ጥሩ ነገር ነው፡፡ የተበላሸውን ባይጠግንም ቢያንስ፣ ቢያንስ ጥፋትን አምኖ ይቅርታ ማለት መሸነፍ ሳይሆን ማሸነፍ ነው፡፡ ዝቅ ማለት ሳይሆን፣ ከፍ ማለት ነው፡፡ የመንፈ...

ቅድስት ድንግል ማሪያም

Image
ቅድስት ድንግል ማሪያም  ከ ‹‹ታማልዳለች›› እና ‹‹አታማልድም ›› በፊት  ( አሌክስ አብርሃም ) የስነ - መለኮት ትምህርት የሚማር ጓደኛየ ‹‹ስለ ድንግል ማሪያም ምድራዊ ቆይታ በአማርኛ የተፃፉ መፅሃፍትን ላክልኝ ›› ስላለኝ በርካታ መንፈሳዊ መፅሃፍ የሚሸጥባቸው ቦታወች ዞር ዞር ብየ የተባልኩትን መፅሃፍ መፈለግ ያዝኩ ! ማግኘት የቻልኩት ግን ከሁለት መፅሃፍት አይበልጡም ! ( በደንብ ባትፈልግ ነው ሞልቷል ትሉኝ ይሆናል ) እውነቱን ለመናገር በራሴም ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ባላቸው ሰወችም ባስፈልግም የተባለው መፅሃፍ እንኳን ሊሞላ ከጠቀስኩት ቁጥር ከፍ ማለት አልቻለም !! በጣም ነው የገረመኝ … ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ፣ስለ ሃዋሪያት ፃድቃን ሰማእታት ፣ መፅሃፍ ቅዱስ ላይ ስማቸው ስለተጠቀሱ ሁሉ መፅሃፍት (በግለሰቦች የተፃፉ ረዳት መፃህፍት ) ገበያው ላይ ለጉድ ታገኛላችሁ . . . ስለድንግል ማሪያም ስትጠይቁ ግን የሚሰጧችሁ መፅሃፍ የሚበዛው በሁለት ፅንፍ ተወጥሮ ወደክርክር የሚያዘነብል ‹‹ማማለድና አለማማለድ›› ላይ ያተኮረ ይዘት ያለው መፅሃፍ ነው ! ለዛውም ራሱን ችሎ ስለድንግል ማሪያም የተፃፈው መፅሃፍ በጣም ትንሽ ነው ‹‹የማማለድና ያለማማለድ ›› ይዘት ያላቸው ቁንፅል ታሪኮች ስለሌሎች መንፈሳዊ ጉዳዮች በተፃፉ መፅሃፍት እንደአንድ ርእስ ሸጎጥ ተደርገው ነው የሚገኙት ! (እስቲ ጎራ ብላችሁ ጠይቁና ታዘቡኝ ) ከዛ ቀን በኋላ ዝም ብየ ሳስብ አይምሮየ ውስጥ የሚመላለሰው ‹‹ ህፃናት ልጆች ስለማሪያም ምን ያስባሉ›› የሚል ጥያቄ ነበር ! ያብስራ የምትባል ፕሮቴስታንት ቤተሰቦች ያሏት ልጅ (አስር አመት ቢሆናት ነው ) አግኝቸ ጠየኳት ‹‹ ያብስራ ! ስለማሪያም የምታውቂውን ንገሪኝ እሰቲ ›› ትንሽ እንኳን ሳታስብ በቀጥታ እ...

ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ

Image
ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ አንድ እግር በርበሬ መንቀል አቅቷችሁ፣ አቃጥሎ ለብልቦ ፈጅቶ ገደላችሁ።በመሳፍንታዊው ዘመን ሳይጠበቅ ብቅ ያለውን መይሳው ካሣ/ ቴዎድሮስን አንዲት ተጎጂ አልቃሽ የገጠመችበት ስንኝ ነው፡፡ አንዷን ኢትዮጵያ ሰላሳ አርባና ሀምሳ ቦታ ቦጫጭቀው ለዕለት ደስታቸው የሚኖሩ መሳፍንት በበዙበት ዘመን አንድ ሰው ተወለደ፡፡ የዚህን ጀግና እትብት የቀረበረች ቋራ እንደምን የታደለች ናት፡፡ ቋራ ከዚያም ቀድሞ የጀግኖች ከዚያም በኋላ የጀግኖች ምድር ናት፡፡ የጥር ወርን በራፍ ታላቁን ምድር እያነሳን እንዘክረዋለን፡፡ አባ ታጠቅ ካሳ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ከ1999 ዓመት በፊት ጥር 6 ቀን 1811 ዓ/ም በጎንደር ቋራ ተወለዱ፡፡ አባታቸው ደጃዝማች ሀይለጊዮርጊስ ከሱዳኖች ጋር በ 1813 ዓም ሲዋጉ በመሞታቸው እናታቸው አትጠገብ ወንድ በወሰን ከቋራ በመሸሽ ወደ ጎንደር ከተማ በሁለት ዓመታቸው ይዘዋቸው መጡ፡፡ ወይዘሮ አትጠገብ የጎንደር ከተማ መስራች የአፄ ፋሲለደስ ዘመድ ናቸው፡፡ ወይዘሮዋ የጎንደር ባላባት ዘር ናቸው እንጂ በታሪክ እንደሚታወቀው ኮሶ ሻጭ አልነበሩም ፡፡ ነገር ግን አፄ ቴዎድሮስን ለማዋረድ የኮሶ ሻጭ ልጅ ሲሉ ጠላቶቻቸው ጠርተዋቸዋል (ጳውሎስ ኞኞ) አፄ ቴዎድሮስ በእናታቸው ወገን ምንም ወንድም ሆነ እህት አልነበራቸውም ፡፡ እናታቸው ደጃዝማቹ ባለቤታቸው እንደሞቱ ወዲያው ቆርበው ስለነበር ሌላ ልጅ አልወለዱም፡፡ለዚህም ነው ቴዎድሮስ አንድ ለናቱ የተባሉት ፡፡ አፄ ቴዎድሮስ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ፤በትውልድ ስማቸው ካሳ ሀይሉ፤በውትድርና ስማቸው ደግሞ መይሳው ካሳ ሲባሉ የዙፋን ስማቸው ዳግማዊ ቴዎድሮስ ነው፡፡ በትውፊት እንደሚነገረው በ15 ኛው መቶ ክፍለዘመን ቀዳማዊ ቴዎድሮስ የተባለ ተወዳጅ ኢትዮጵያዊ ን...

አንች ስትቀጥሪኝ

Image
** * አንች ስትቀጥሪኝ *** (በሙሉጌታ አንበርብር) የነተበ ልብሴን ወደዚያ ወርውሬ ሻንጣየ ገብቸ ባዲሱ ቀይሬ እመጣልሽለሁ አንች ከጠብቅሽኝ ዘግይቸ አላውቅም አንች ስትቀጥሪኝ ግዴለም ግዴለም ሻንጣየ ይሞላ በአደፋ ጨርቅ አንችጋ ስመጣ ይመስለኛን ወርቅ ኩታየን ለብሸ ወርቄን አገልድሜ እመጣልሽለሁ ሰከንድ ደቂቃ ምታቸው ሳይጨምር እደርስልሻለሁ አንች ስትቀጥሪኝ ወንዙን ተሻግሬ ባህርን ቀዝፌ ተራራን ሰንጥቄ ኮረብታን አልፌ ካለሽበት ቦታ በሰከንዳድ እድሜ እደርስልሻለሁ ምክንያቱም ከራሴ አስበልጨ እኔ እወድሽለሁ አንች ስትቀጥሪኝ አበባ በለለበት በደረቀ ምድረ በዳ መዓዛ ያውደኛል ያውም የፅጌረዳ መዓዛ ያለው ነገር ሽታ ያለው ነገር አንች እንደምትወጅው እኔም እወዳለሁ ምክንያቱም አንች የወደድሽው እኔም እወዳለሁ አንች ስትቀጥሪኝ አንች የምትወጃት ጨረቃ ብጠፋ ገበሬ የሚወደው ዝናቡ ቢያካፋ ኤርፖርት የሚጠላው ጉሙ ቢንሰራፋ ወንዝ ተሻጋሪ ሁሌም የሚጠላው ፈፋ ቢደነፋ ከማሪያም መቀነት ይበልጥ ወድሻለሁ ምክንያቱም የማሪያም መቀነት መዳሰስ እሻለሁ መዳሰሱን ብሻም ሁልጊዜ ብሳሳም እንዳንች መዳሰስ አይቻለኝ መሳም:: አንች ስትቀጥሪኝ * * * * አንች ስትቀጥሪኝ * * * * አንች ስትቀጥሪኝ * * * * @ ላሊበላ  11/11/2008 E.C

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ

Image
ዳግማዊ አፄ ምኒልክ      ዳግማዊ ምኒልክ ከዘመናዊነት ጋር ተያይዘው ከሚነሱባቸው ነገሮች መካከል አንዱ ፎቶግራፍ ይገኝበታል፡፡ ፎቶግራፍና ኢትዮጵያ የተዋወቁት በርሳቸው ዘመን እንደሆነ ይወሳል፡፡ በታሪክ እንደተመዘገበው ፎቶግራፍ አንሺ ከካሜራው ጋር ኢትዮጵያ የገባው በ1875 ዓ.ም. ነው፡፡ : በወቅቱ የነበሩት ኣማካሪዎች አንደዘገቡት አና ቡሃላም በ በጳውሎስ ኞኞ ተተርጉሞ አንደቀረበው ዓጼ ምኒልክ አንድ ቀን የውጭ አማካሪያቸውን ጠሩትና “አንድ ነገር ሰማሁ። ይሄ የሰማሁት ነገር እኔን ትንሽ ያደርግና ከነቤተመንግስቴ፣ ሌላው ቤት ሁሉ፣ ህዝቡ፣ በቅሎና እና ፈረሱ ሁሉ ሳይቀር ከትንሽ ጥቁር ሳጥን ውስጥ ይጨምረናል አሉ። ይሄ ነገር ፈፅሞ የማይቻል ነገር ነው እንዴት ሊሆን ይችላል?” አሉት። : ከዚህ በሇላ ካሜራ እንዲመጣ ታዞ ካሜራው ከነ ፎቶግራፍ አንሺው በ1875 ዓ.ም. መጣ። የፎቶግራፍ ማንሻው አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ ዓጺ ምኒልክ ፎቶ እንዳይነሱ ቀሳውሥቱ አስፍራርተዋቸው ነበር። ሆኖም ግን ዓጼ ምኒልክ ምክራቸውን ወደ ጎን በመተው የመጀመርያውን ፎቶ በግንቦት 13 ቀን 1875 ዓ/ ም ተነሱ። ምኒልክ የመጀመሪያ ፎቶግራፍ የተነሡት ግንቦት 13 ቀን 1875 ዓ.ም. መሆኑንና የቤተ መንግሥት ፎቶግራፍ አንሺ ሆኖ የገባው ቦያጂያን ከሁለት ዓመት በኋላ የሕዝብ ፎቶግራፍ ማንሳት ሱቅን መክፈቱ በጳውሎስ ኞኞ በተዘጋጀው ‹‹አጤ ምኒልክ›› መጽሐፍ ውስጥ ሰፍሯል፡ ዓጼ ምኒልክ ፎቶ ከመነሳት አለፈው ፎቶ ማንሳት እና ማጠብም ጭምር ተምረው እንደነበር ይታወቃል። : መጀመሪያው ክሊኒክና ፋርማሲ በ1889 ዓ.ም. በቤተ መንግሥታቸው ውስጥ ያቋቋሙት ዳግማዊ ምኒልክ ናቸው፡፡ በዓድዋው ጦርነት ምክንያት ከሩሲያ ቀይ መስቀል ማኅበር የተላኩት ሐኪሞች ...

የምንወደው ሰው በሞት ከተለየን በኋላ የመጀመሪያው በአል

Image
የምንወደው ሰው በሞት ከተለየን በኋላ የመጀመሪያው በአል _____________________________ የበዓል ቀን ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር አብሮ ለማሳለፍ ጥሩ ጊዜ ነው፡፡ በቅርቡ የምንወደውን ሰው አጥተን ከሆነ በዓል የሀዘን ስሜት የሚባባስበት ወቅት ሊሆን ይችላል ፡፡ ሀዘን ቀላል አይደለም በተለይ ቅርብ የሆነን ሰው ካጣን በኋላ ያለውን የመጀመሪያ በዓል ማሳለፍ አስቸጋሪና የተዘበራረቀ ስሜት ይፈጥራል፡፡ በሀዘን ውስጥ ሆነው በዓል ለሚያከብሩ የሚከተሉት ነጥቦች ደህና ሆነው እንዲያሳልፉ ይረዳሉ፡፡ • ትዝታዎችን ከቅርብ ሰዎች ጋር መጋራት፦ ያጣነው ሰው አለመኖር ካልተወራ ሀዘኑ ጠልቆ ይሰማል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የእህት፣የወንድም፣የእናት ወይም የአባት ሀዘንን ላለመቀስቀስ ያረፈው ሰው ስም አይነሳም፡፡ ከዝምታ ይልቅ ያሳለፏቸውን የበዓልም ሆነ ሌሎች ትዝታዎች መጋራቱ ይረዳል፡፡ የሚያስቁ ገጠመኞችን፤ ያደርጉ የነበረውን ነገሮች መነጋገሩ ሙሉ ለሙሉ ኖርማልና እርም ለማውጣት የሚያግዙ ነገሮች ናቸው፡፡በተጨማሪም የሚሰማንን ስሜት መግለፅ፣ አብረን ያሳለፍናቸውን ጥሩ ጊዜያት ማስታወስ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ከፍተኛ የሆነ ተስፋ መቁረጥና ብቸኝነት ወደ ራስን መጉዳትና አብዝቶ አልኮል መጠቀም እንዳያስከትል መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ የሚሰማንን ስሜት ከሚጋሩ ሰዎች ጋር አብሮ ማሳለፍ የብቸኝነት ስሜትን ይከላከላል፡፡ •የበዓል ግዴታዎችን መቀነስ፦ በዓላት ሲመጡ ግዴታዎች ተከትለዋቸው ይመጣሉ፡፡ ለምሳሌ፡- ዘመድ መጠየቅ፣ስጦታ መስጠት፣የመስሪያ ቤት ዝግጅቶች የመሳሰሉት፡፡ ተያይዞ የሚመጣውን ጫና ለመቀነስ ለራስ ጊዜ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ተገልሎ ብቸኛ መሆን ሳይሆን ጫና የሚፈጥሩ ግዴታዎችን መቀነስ ጥሩ ነው፡፡ ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ ባንፈልግ ሰዎች በሀዘኑ ምክ...